am_tn/jdg/18/21.md

1.9 KiB

ትንንሾቹን ልጆች ከፊት ለፊታቸው አደረጓቸው

በዚህ መልኩ የሚጓዙት ልጆቹን ለመጠበቅ ነው። ሚካና ሰዎቹ ቢያጠቋቸው መጀመሪያ የሚያገኙት ጦረኞቹን እንጂ ልጆቹን አይሆንም። አ.ት፡ “ትንንሾቹን ልጆች ለመጠበቅ ከፊት ለፊታቸው አደረጓቸው”

በጥሩ ርቀት

“ጥቂት ርቀት”፣ ይህ ለመለካት የሚበቃውን ርዝመት አጭር ርቀት ይለዋል። (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)

በሚካ ቤት አቅራብያ ባሉት ቤቶች ውስጥ የነበሩ ሰዎች አንድ ላይ ተጠርተው ነበር

ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “በቤቱ አቅራቢያ ባሉ ቤቶች ውስጥ የነበሩትን ሰዎች አንድ ላይ ጠራቸው” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)

በዳን ሰዎች ላይ ደረሱባቸው

ይህ ከኋላ ተከትለዋቸው እንደሮጡ ያመለክታል። ይህ በግልጽ ሊነገር ይችላል፝። አ.ት፡ “ከዳን ሰዎች ኋላ በመሮጥ ደረሱባቸው”

ወደ ኋላቸው ተመለሱ

“የዳን ሰዎች የሆኑት ወደ ኋላቸው ዞሩ”

ተጠራርታችሁ የተሰባሰባችሁት ለምንድነው?

ይህ የወቀሳ ጥያቄ ነው። እንደ መግለጫ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “እኛን ለማሳደድ ሰዎችህን ጠርተህ መሰብሰብ አልነበረብህም”። (ምላሽ የማይሻ ጥያቄ የሚለውን ተመልከት)

አንድ ላይ ተጠርተው ነበር

ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “እነዚህን ሰዎች አንድ ላይ ጠሯቸው” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)