am_tn/jdg/18/09.md

1.5 KiB

ምንም እየሠራህ አይደለም?

ይህ ምላሽ የማይፈልግ ጥያቄ የተጠየቀው በአሽሙር ሲሆን ትርጉሙም ተቃራኒውን ማድረግ ነበረባቸው የሚል ነው። ይህ ጥያቄ እንደ መግለጫ ሊጻፍ ይችላል። አ.ት፡ “አሁን የሆነ ነገር ማድረግ አለባችሁ” (ምላሽ የማይሻ ጥያቄ እና ድርብ አሉታ የሚለውን ተመልከት)

ለማጥቃት የዘገያችሁ አትሁኑ

እነዚህ “አትሁኑ” እና “አትዘግዩ” የሚሉት አሉታዊ ቃላቶች በአንድ ላይ በቶሎ እንዲያጠቁ አዎንታዊ አሳብ ላይ አጽንዖት የሰጣሉ። “ፍጠኑ! አጥቁ” (ድርብ አሉታ የሚለውን ተመልከት)

ምድሪቱ ሰፊ ናት

“ምድሪቱ ታላቅ ናት” ይህ የምድሩን መጠን ይገልጻል።

ምድሪቱ ምንም ነገር ያልጎደላት

ሰዎቹ ለመኖር በጣም ተመራጭ ቦታ እንደሆነ አጽንዖት ለመስጠት ግነትን ተጠቅመዋል። አ.ት፡ “በዚያ የሚያስፈልገን ነገር ሁሉ ይኖረናል” (ግነት እና ጥቅል አስተያየት የሚለውን ተመልከት)

ምንም ነገር ያልጎደለው

ሁለቱ አሉታዊ ቃላት በአንድነት አዎንታዊ አሳብ ላይ አጽንዖት ይሰጣሉ። አ.ት፡ “ሁሉም ነገር ያለው” (ድርብ አሉታ የሚለውን ተመልከት)