am_tn/jdg/18/01.md

1.7 KiB

በእነዚያ ቀናት

ይህ ሐረግ በታሪኩ ፍሰት ላይ ሌላ አዲስ የሁነት ጅማሬን ያስተዋውቃል። (አዲስ ሁነትን ማስተዋወቅ የሚለውን ተመልከት)

በእነዚያ ቀናት… ከእስራኤል ነገዶች መካከል

ይህ ስለ እስራኤልና ስለዳን ነገድ ሕዝቦች ዳራዊ መረጃ ነው። (ዳራዊ መረጃ የሚለውን ተመልከት)

ምንም ርስት አልተቀበለም

ይህ በግልጽ የሚኖሩበትን መሬት እንዳልወረሱ ያመለክታል። አ.ት፡ “የመሬት ርስት አልተቀበልንም”

ከነገዳቸው በሙሉ

“በሙሉ” የሚለው ቃል በነገዱ ያሉትን ሰዎች ሁሉ ያመለክታል። አ.ት፡ “በየነገዱ መካከል ካሉት ሰዎች ሁሉ” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

ልምድ ያላቸው ጦረኞች

“ልምድ ያላቸው ተዋጊዎች”

ጾርአ

የዚህን ከተማ ስም በመስፍንት 13፡2 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት።

ኤሽታኦል

የዚህን ከተማ ስም በመሳፍንት 13፡25 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት።

ምድሪቱን በእግር ተጉዘው እንዲሰልሉ

“በእግር” የሚለው ሐረግ መራመድ ማለት ነው። አ.ት፡ “በእርሱ ላይ በመራመድ መሰለል” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)

ሚካ

የዚህን ሰው ስም በመሳፍንት 17፡1 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት