am_tn/jdg/16/10.md

1.3 KiB

እንደዚህ ነው ያታለልከኝና የዋሸኸኝ

ማታለልና መዋሸት ተመሳሳይ ሲሆኑ ደሊላ ምን ያህል እንደተናደደች አጽንዖት ለመስጠት ተነግረዋል። አ.ት፡ “እጅግ አታልለኸኛል!”

ልትሸነፍ የምትችለው

ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “ሰዎች ሊያሸንፉህ የሚችሉት”

ፍልስጤማውያን ባንተ ላይ ናቸው

“ባንተ ላይ” የሚለው ሐረግ ሊይዙት ተዘጋጅተዋል ማለት ነው። አ.ት፡ “ፍልስጥኤማውያኑ ሊይዙህ እዚህ ናቸው” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)

ተቀምጠው ይጠባበቁት ነበር

ይህ ማለት ተደብቀው ለማጥቃት ትክክለኛውን ጊዜ እየጠበቁ ነበር ማለት ነው። አ.ት፡ “ሊያጠቁት እየጠበቁ” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)

የክር ቁራጭ እንደሆኑ ያህል

ደራሲው ሳምሶን ክርን እንደሚበጣጥስ በቀላሉ ገመዶቹን እንደበጣጠሰ በማነጻጸር ያብራራል። አ.ት፡ “የክር ቁራጭ የሆኑ ያህል በቀላሉ”