am_tn/jdg/15/17.md

1.8 KiB

ራማት ሌሒ

ይህ የቦታ ስም ነው። ስሙም “የመንጋጋ ኮረብታ” ማለት ነው። (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)

በጣም ተጠምቶ ነበር

“ውሃ መጠጣት በጣም አስፈለገው”

ነገር ግን አሁን በውሃ ጥም ሞቼ ባልተገረዙት. . . እወድቃለሁ?

ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች 1) ሳምሶን በጣም ከመጠማቱ የተነሳ የምር ሊሞት እንደሆነ። አ.ት፡ “ነገር ግን አሁን በጥም እሞታለሁ፣ ሰውነቴም ባልተገረዙት … ይወድቃል”። ወይም 2) ሳምሶን በጥም ይሞት እንደሆነ በመጠየቅ ምን ያህል እንደተጠማ ያጋንናል። አ.ት፡ “ነገር ግን አሁን በጥሜ ምክንያት እንድደክም፤ ባልተገረዙትም … እንድወድቅ ትፈቅዳለህ?” (ግነት እና ጥቅል አስተያየት የሚለውን ተመልከት)

በጥም መሞት

ይህ ማለት በቂ ውሃ ባለመጠጣትህ ምክንያት በሰውነትህ ውስጥ በቂ ውሃ አጥተህ መሞት ማለት ነው። (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)

በእነዚያ ባልተገረዙት እጅ መውደቅ

“በእጃቸው መውደቅ” የሚለው ሐረግ መማረክ ማለት ነው። “እነዚያ ያልተገረዙ” የሚለው ፍልስጤማውያንን ሲሆን “ያልተገረዘ” የሚለው ቃል እግዚአብሔርን የማያመልኩ ስለመሆናቸው አጽንዖት የሚሰጥ ቃል ነው። አ.ት፡ “እግዚአብሔርን በማያውቁ ፍልስጥኤማውያን መማረክ” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)