am_tn/jdg/15/14.md

1.3 KiB

በመጣ ጊዜ

ሳምሶን ብቻውን እልተጓዘም፤ በገመድ ባሰሩት ሰዎች እየተመራ ነበር። አ.ት፡ “በመጡ ጊዜ”

ሌሒ

ይህ በይሁዳ የሚገኝ ከተማ ስም ነው። ይህንን በመሳፍንት 15፡9 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት።

በእርሱ ላይ በኃይል መጣበት

“በላዩ ላይ መጣበት” የሚለው ሐረግ የእግዚአብሔር መንፈስ ሳምሶን ላይ ተጽዕኖ አሳድሯል ማለት ነው። በዚህ ቦታ፤ በጣም ብርቱ አድርጎታል። አ.ት፡ “ሳምሶንን በጣም ብርቱ አደረገው” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)

በክንዱ ላይ የነበሩት ገመዶች እንደ ተቃጠለ ፈትል ሆኑ

ሳምሶን እጁ የታሰረበትን ገመድ በቀላሉ በጣጥሶታል። ደራሲው ገመዱን እንዴት በቀላሉ እንደበጣጠሰው ለመግለጽ እንደተቃጠለ ፈትል ይለዋል። አ.ት፡ ”በክንዱ ላይ ያሉትን ገመዶች ፈትል በቀላሉ እንደሚቃጠል በጣጠሳቸው”

የተልባ ፈትል

ከተልባ ተክል የሚገኝ ቃጫና ክር ጨርቅ ለመስራት ይጠቅማል።