am_tn/jdg/15/11.md

1.3 KiB

የይሁዳ ሶስት ሺህ ወንዶች

“3000 የይሁዳ ወንዶች” (ቁጥሮች የሚለውን ተመልከት)

በኢታም ገደል ያለ ዋሻ

ይህንን ሐረግ በመሳፍንት 15፡8 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት።

ፍልስጥኤማውያን በእኛ ላይ ገዢዎች እንደሆኑ አታውቅም? በእኛ ላይ ያደረከው ይህ ምንድን ነው?

የይሁዳ ሰዎች እነዚህን ጥያቄዎች የሚጠይቁት ሳምሶንን ለመገሰጽ ነው። እነዚህ ጥያቄዎች እንደ መግለጫ ሊጻፉ ይችሉ ይሆናል። አ.ት፡ “ፍልስጤማውያን በኛ ላይ ገዢዎች እንደሆኑ ታውቃለህ ነገር ግን አንተ የምታደርገው እንዳልሆኑ ያህል ነው። ያደረከው ነገር ከባድ ጉዳት አምጥቶብናል።” (ምላሽ የማይሻ ጥያቄ የሚለውን ተመልከት)

አደረጉብኝ፥ ስለዚህ እኔም አደረግሁባቸው

ሳምሶን ሚስቱን እንዴት እንደገደሉበትና እርሱ በበቀል እንዴት እንደገደላቸው እያመለከተ ነው። ይህ በግልጽ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “ሚስቴን ገድለዋታል፤ ስለዚህ እኔም ገደልኳቸው።”