am_tn/jdg/15/01.md

1.6 KiB

ራሱን ጠየቀ

ይህ ማሰብን ያመለክታል። አ.ት፡ “በራሱ አሰበ” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)

ወደ ሚስቴ ክፍል እሄዳለሁ

ሳምሶን ከሚስቱ ጋር ለመተኛት አስቦ ነበር። ይህ በግልፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “አብረን እንድንተኛ ወደ ሚስቴ ክፍል አሄዳለሁ”

እንዲገባ አልፈቀደለትም

ሳምሶን ለራሱ ከተናገረው ውስጥ “የእርሷ ክፍል” የሚለውን ሐረግ መረዳት ይቻላል። ይህ እዚህ ጋር መደገም ይችላል። አ.ት፡ “ወደ ክፍሏ እንዲገባ አልፈቀደለትም”

ስለዚህ ለጓደኛህ ሰጠኋት

ይህ ማለት ሚስት እንድትሆነው ለጓደኛው ሰጣት ማለት ነው። ይህ በግልፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “ከእርሱ ጋር እንድትጋባ ለጓደኛህ ሰጠኋት”

አይደለችምን?

ይህን ጥያቄ የሚጠይቀው ሳምሶን ከእርሱ ጋር ሊስማማ እንደሚገባ ለማመልከት ነው። ይህ ጥያቄ እንደ መግለጫ ሊጻፍ ይችላል። አ.ት፡ “እንደምትስማማ ተስፋ አደርጋለው”። (ምላሽ የማይሻ ጥያቄ የሚለውን ተመልከት)

በምትኳ ውሰዳት

ሳምሶን እንደ ሚስቱ እንዲወስዳት አስተያየት እየሰጠ ነው። ይህ በግልፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “በእርሷ ምትክ ሚስት እንድትሆንህ ውሰዳት”