am_tn/jdg/14/19.md

1.6 KiB

በሳምሶን ላይ በኃይል መጣበት

“መጣበት” የሚለው ቃል ትርጉሙ የእግዚአብሔር መንፈስ ሳምሶን ላይ ተጽዕኖ አሳደረበት ማለት ነው። በዚህ ጉዳይ፣ በኃይል አበረታው። አ.ት፡ “የእግዚአብሔር መንፈስ በኃይል አበረታው” ወይም “ሳምሶንን በጣም ኃይለኛ አደረገው” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)

ከሰዎቻቸው ሠላሳውን ገደለ

“ከሰዎቻቸው 30 ገደለ” (ቁጥሮች የሚለውን ተመልከት)

ከሰዎቻቸው

በዚያ የሚኖሩትን ሰዎች”

ብዝበዛ

አብዛኛውን ጊዜ ከውጊያ ወይም ከጦርነት በኋላ በኃይል የሚወሰዱ ነገሮች

ልብሶቻቸውን

እነዚህ ከአስቀሎና የወሰዳቸው ብዝበዛዎቹ ነበሩ። አ.ት፡ “የወሰዳቸውን ሙሉ ልብሶች”

በቁጣ ነዶ

“በጣም ተናዶ”

ወደ አባቱ ቤት ወጣ

እዚህ ጋ የአባቱ ቤት ከሚገኝበት አካባቢ ሳምሶን የነበረበት ተምና የመሬት አቀማመጡ ዝቅ ያለ ስለነበረ “ወጣ” የሚለው ቃል ጥቅም ላይ ውሏል።

የሳምሶን ሚስት ለቅርብ ጓደኛው ተሰጠች

ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “የሚስቱ አባት እርሷን ለቅርብ ጓደኛው ሰጣት” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)

የቅርብ ጓደኛ

“ከሌላው የቀረበ ጓደኛ”