am_tn/jdg/12/03.md

2.8 KiB

እናንተ አላዳናችሁኝም

“እናንተ” የሚለው ቃል ብዙ ቁጥር ሲሆን የኤፍሬምን ሰዎች ያመለክታል። ዮፍታሔ “እኔ” በሚልበት ጊዜ የሚያመለክተው ራሱን ጨምሮ የገለዓድን ሰዎች ነው። አ.ት፡ “አላዳናችሁንም”።

ሕይወቴን በእጄ ጥዬ

ይህ የአነጋገር ዘይቤ በራስ ጉልበት በመደገፍ ራስን ለአደጋ መስጠት ማለት ነው። ዮፍታሔ የገለዓድን ሰዎች እንደ ራሱ አድርጎ ማመልከቱን ይቀጥላል። አ.ት፡ “በራሳችን በመተማመን ሕይወታችንን ለአደጋ ሰጥተናል”። (የአነጋገር ዘይቤ እና የሚለውን ተመልከት)

እግዚአብሔር ድልን ሰጥቶኛል

በአሞናውያን ላይ እግዚአብሔር ለገለዓድ ሰዎች ድልን እንደ ሰጣቸው ዮፍታሔ ያመላክታል። የዚህ መግለጫ ሙሉ ትርጉም በይበልጥ መብራራት ይችላል። አ.ት፡ “በእነርሱ ላይ እግዚአብሔር ድልን ሰጥቶናል” ወይም “በጦርነት እንድናሸንፋቸው እግዚአብሔር ፈቅዶልናል”

ከኤፍሬም ጋር ተዋጋ

“እርሱ” የሚለው ቃል የሚያመለክተው ዮፍታሔንና የገለዓድን ተዋጊዎች ሁሉ ነው። አ.ት፡ “ከኤፍሬም ጋር ተዋጉ”

ለምን ልትወጉኝ መጣችሁ

“እናንተ” የሚለው ቃል ብዙ ቁጥር ሲሆን የሚያመለክተው የኤፍሬምን ሰዎች ነው። ዮፍታሔ “እኔ” በሚልበት ጊዜ የሚያመለክተው ራሱን ጨምሮ የገለዓድን ሰዎች ነው። አ.ት፡ “እኛን ልትወጉን ለምን መጣችሁ”

ገለዓዳውያን ኮብላዮች ናቸው

የዚህን ስድብ ትርጉም ግልጽ ልታደርገው ትችላለህ። አ.ት፡ “ይህ ቦታ ለእናንተ ለገለዓዳውያን አይገባችሁም። እናንተ በዚህ ለመኖር የመጣችሁ ሰዎች ብቻ ናችሁ”

በአሞን ሰዎች ላይ አልፈው ሄዱ

ይህ ማለት በአሞን በኩል ሲያልፉ ከአሞናውያን ጋር ተዋጉ። የዚህ መግለጫ ሙሉ ትርጉም ግልጽ መደረግ ይችላል። አ.ት፡ “በግዛታቸው በኩል ስናልፍ ክአሞን ሰዎች ጋር ተዋጋን”

ገለዓዳውያን

የገለዓድ ሰዎች

በኤፍሬም -- በኤፍሬምና በምናሴ

“በኤፍሬምና በምናሴ አውራጃዎች” ወይም “በኤፍሬምና በምናሴ ምድር”። እዚህ ጋ “ኤፍሬም” እና “ምናሴ” የሚያመለክቱት አውራጃዎችን ሲሆን በዚያ በሚኖሩ ነገዶች ስም ተሰይመዋል።