am_tn/jdg/12/01.md

1.4 KiB

ለኤፍሬም ሰዎች ጥሪ ደረሳቸው

እዚህ ጋ “ጥሪ” የሚለው የነገር ስም እንደ ግሥ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “የኤፍሬም ሰዎች በአንድ ላይ ተጠሩ” ወይም “የኤፍሬም ሰዎች ወታደሮቻቸውን በአንድ ላይ ሰበሰቧቸው”። (የነገር ስም የሚለውን ተመልከት)

ጻፎን

ይህ የአንዲት ከተማ ስም ነው። (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)

ተሻገሩ -- አለፉ

“መንገዳቸውን … አልፈው ሄዱ” ወይም “ጉዞአቸውን … አልፈው ተጓዙ”

ቤትህን በላይህ ላይ እናቃጥለዋለን

ይህ የአነጋገር ዘይቤ የሚያመለክተው ቤቱን በውስጡ ካሉት ሰዎች ጋር ስለ ማቃጠል ነው። አ.ት፡ “ቤትህን በውስጡ እንዳለህ እናቃጥለዋለን”። (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)

እናንተን በጠራዃችሁ ጊዜ

እዚህ ጋ “እናንተ” የሚለው ቃል ብዙ ቁጥር ሲሆን የሚያመለክተው የኤፍሬምን ሰዎች ነው።

አላዳናችሁኝም

ዮፍታሔ “እኔ” የሚለውን ቃል የሚጠቀመው ራሱንና የገለዓድን ሰዎች በሙሉ ለማመልከት ነው። አ.ት፡ “አታድኑን”