am_tn/jdg/11/26.md

1.9 KiB

ሦስት መቶ ዓመት

“300 ዓመት” (ቁጥሮች የሚለውን ተመልከት)

ሐሴቦን

በመሳፍንት 11፡19 ላይ በተረጎምክበት መልኩ የዚህችን ከተማ ስም ተርጉም።

አሮዔር

ይህ የአንዲት ከተማ ስም ነው። (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)

አርኖን

በመሳፍንት 11፡13 ላይ በተረጎምክበት መልኩ የዚህችን ከተማ ስም ተርጉም።

ታዲያ በዚያን ጊዜ ለምን አላስመለስካቸውም?

ዮፍታሔ ምላሽ በማይሻ ጥያቄ የአሞናውያንን ንጉሥ እየገሰጸው ነው። ይህ ጥያቄ እንደ መግለጫ ሊተረጎም ይችላል። አ.ት፡ “በዚያን ጊዜ ማስመለስ ነበረብህ” ወይም “ከአመታት በፊት ልታስመልሳቸው ይገባህ ነበር፤ አሁን ግን በጣም ዘግይተሃል” (ምላሽ የማይሻ ጥያቄ የሚለውን ተመልከት)

እኔ አልበደልኩህም፣ አንተ ግን እየወጋኸኝ በድለኸኛል

ዮፍታሔ የሚናገረው ሴዎንን ነው። እዚህ ጋ፣ ዮፍታሔ፣ ራሱን እንደ እስራኤላውያን፣ ንጉሣቸውን ሴዎንን እንደ አሞናውያን አድርጎ ይናገራል። አ.ት፡ “እስራኤላውያን ሕዝብህን አልበደሉም፣ ይሁን እንጂ ሕዝብህ እየወጉን በድለውናል”።

አልበደልኩህም -- በድለኸኛል

ይህ የአነጋገር ዘይቤ ነው። አንድን ሰው መበደል ማለት እነርሱን መበደል ነው። አ.ት፡ “የማይገባውን አላደረግሁብህም … የማይገባውን አድርገህብኛል” ወይም “ኢፍትሐዊ አልሆንኩብህም … ኢፍትሐዊ ሆነህብኛል”። (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)