am_tn/jdg/11/23.md

2.8 KiB

አሁን መሬታቸውን የራስህ አድርገህ ትወስዳለህ?

ዮፍታሔ ምላሽ በማይፈልግ በዚህ ጥያቄ የአሞናውያንን ንጉሥ ይገስጸዋል። “የእነርሱ” የሚለው ቃል እስራኤልን ያመለክታል። ይህ ጥያቄ እንደ መግለጫ ሊተረጎም ይችላል። አ.ት፡ “በመሆኑም፣ መሬታቸውን የራስህ አድርገህ መውሰድ አይኖርብህም”። (ምላሽ የማይሻ ጥያቄ የሚለውን ተመልከት)

አምላክህ ካሞሽ የሚሰጥህን ምድር አትወስድም?

ዮፍታሔ ምላሽ በማይሻ ጥያቄ የአሞናውያንን ንጉሥ እየገሰጸው ነው። ይህ ጥያቄ እንደ መግለጫ ሊተረጎም ይችላል። አ.ት፡ “አምላክህ ካሞሽ የሚሰጥህን ምድር ብቻ መውሰድ ይኖርብሃል”። (ምላሽ የማይሻ ጥያቄ የሚለውን ተመልከት)

ውሰድ

ይህ የአነጋገር ዘይቤ ሲሆን ትርጉሙ አንድን ነገር በቁጥጥር ስር ማድረግ ማለት ነው። አ.ት፡ “በቁጥጥርህ ስር አድርግ” ወይም “የራስህ አድርግ”። (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)

ካሞሽ

ይህ የሐሰተኛ አምላክ ስም ነው። (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)

አሁን አንተ ከሞዓብ ንጉሥ ከሴፎር ልጅ ከባላቅ በእርግጥ ትበልጣለህ?

ዮፍታሔ ምላሽ በማይሻ ጥያቄ የአሞናውያንን ንጉሥ እየገሰጸው ነው። ይህ ጥያቄ እንደ መግለጫ ሊተረጎም ይችላል። አ.ት፡ “አንተ የሞዓብ ንጉሥ ከነበረው ከሴፎር ልጅ ከባላቅ አትሻልም” (ምላሽ የማይሻ ጥያቄ የሚለውን ተመልከት)

ባላቅ -- ሴፎር

እነዚህ የሰዎች ስምች ናቸው። (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)

ከእስራኤል ጋር ለመከራከር ደፍሯል?

ዮፍታሔ ምላሽ በማይሻ ጥያቄ የአሞናውያንን ንጉሥ እየገሰጸው ነው። ይህ ጥያቄ እንደ መግለጫ ሊተረጎም ይችላል። አ.ት፡ “ይሁን እንጂ ከእስራኤል ጋር ለመከራከር አልደፈረም”። (ምላሽ የማይሻ ጥያቄ የሚለውን ተመልከት)

በእነርሱስ ላይ ጦርነትን ዐውጇል?

ዮፍታሔ ምላሽ በማይሻ ጥያቄ የአሞናውያንን ንጉሥ እየገሰጸው ነው። ይህ ጥያቄ እንደ መግለጫ ሊተረጎም ይችላል። አ.ት፡ “ከቶ በእነርሱ ላይ ጦርነትን አላወጀም”። (ምላሽ የማይሻ ጥያቄ የሚለውን ተመልከት)