am_tn/jdg/10/10.md

1.8 KiB

የእስራኤል ሕዝብ ወደ እግዚአብሔር ጮኹ

ይህ ማለት የእስራኤል ሕዝብ እግዚአብሔር እንዲረዳቸው በፍጹም ልባቸው ጠየቁት።

አምላካችንን በመተዋችን ምክንያት

ከዚያ በኋላ እግዚአብሔርን አለማምለካቸውና አለመታዘዛቸው ሰዎቹ እግዚአብሔርን ትተው ወደ አንድ የሆነ ቦታ እንደሄዱ ሆኖ ተነግሯል። ( ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

አምላካችንን ትተነዋል

ሕዝቡ የሚናገሩት ስለ እግዚአብሔር ሲሆን “አምላካችን” ብለው ይጠሩታል። ይህ በሁለተኛ መደብ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “አምላካችን ሆይ፣ አንተን ትተንሃል” (አንደኛ፣ ሁለተኛ፣ ወይም ሦስተኛ መደብ የሚለውን ተመልከት)

ሲዶናውያን -- አላዳንኋችሁምን?

ሌሎች አማልክትን ስለማምለካቸው እግዚአብሔር የእስራኤልን ሕዝብ ይገስጻቸዋል። ይህ መልስ የማይሻ ጥያቄ እንደ መግለጫ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “ከሲዶናውያን … ያዳንኋችሁ እኔ ነኝ” (መልስ የማይሻ ጥያቄ የሚለውን ተመልከት)

ማዖናውያን

እነዚህ ከማዖን ቤተሰብ ወይም ጎሳ የሆኑ ሕዝቦች ናቸው። (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)

ከኃይላቸው

እዚህ ጋ “ኃይል” የሚወክለው አማሌቃውያንን እና ማዖናውያንን ነው። አ.ት፡ “ከእነርሱ”። (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)