am_tn/jdg/10/08.md

1.5 KiB

አደቀቋቸውና አስጨነቋቸው

እነዚህ ሁለት ቃላት የሚሉት በመሠረቱ ስለ አንድ ነገር ሲሆን እስራኤላውያን ምን ያህል እንደተሰቃዩ አጽንዖት ለመስጠት ነው። አ.ት፡ “በከፋ ሁኔታ አስጨነቋቸው”

አሥራ ስምንት ዓመት

“18 ዓመት” (ቁጥሮች የሚለውን ተመልከት)

ከዮርዳኖስ ማዶ የነበሩት

ይህ ማለት ከዮርዳኖስ ወንዝ በስተምስራቅ ማለት ነው።

በገለዓድ ያለው

“ይህ አውራጃም ደግሞ ገለዓድ ተብሎ ተጠርቷል”

ይሁዳ - ብንያም

“ይሁዳ” እና “ብንያም” የእነዚያን ነገዶች ሕዝቦች ያመለክታል። አ.ት፡ “የይሁዳ ነገድ ሕዝቦች … የብንያም ነገድ ሕዝቦች”። (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

የኤፍሬም ቤት

እዚህ ጋ “ቤት” የሚያመለክተው የኤፍሬምን ነገድ ሕዝቦች ነው። አ.ት፡ “የኤፍሬም ነገድ ሕዝቦች”። (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

በመሆኑም እስራኤል እጅግ ተጨነቀ

“እስራኤል” የሚያመለክተው የእስራኤልን ሕዝብ ነው። አ.ት፡ “በመሆኑም የእስራኤል ሕዝብ በጣም ተሰቃየ”። (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)