am_tn/jdg/10/06.md

2.4 KiB

በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ማድረጋቸውን አበዙ

አንድ ሰው እየጨመረበት እንደሚያተልቀው አንዳች ነገር ይህ የተነገረው ስለ ክፋት ነው። አ.ት፡ “እግዚአብሔር ክፉ ነው ያለውን ማድረጋቸውን ቀጠሉ”። (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

በእግዚአብሔር ፊት

የእግዚአብሔር ፊት የሚወክለው የእርሱን ፍርድ ወይም ምዘና ነው። አ.ት፡ “እግዚአብሔር እንደሚለው” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

አስታሮቶች

ይህ የአስታሮት ብዙ ቁጥር ሲሆን በተለያየ ቅርጽ የምትመለክ እንስት አምላክ ነበረች። ይህንን በመሳፍንት 2፡13 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት።

እግዚአብሔርን ተዉት፣ አላመለኩትምም

በመሠረቱ ደራሲው ሁለት ጊዜ የተናገረው ስለ አንድ ነገር አጽንዖት ለመስጠት ነው። እነዚህ ሊጣመሩ የሚችሉ ናቸው። አ.ት፡ “እግዚአብሔርን ማምለካቸውን ሙሉ በሙሉ አቆሙ”

እግዚአብሔርን ተዉት

ከዚያ በኋላ እግዚአብሔርን አለማምለካቸውና አለመታዘዛቸው ሰዎቹ እግዚአብሔርን ትተው ወደ አንድ የሆነ ቦታ እንደሄዱ ሆኖ ተነግሯል። (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

በእስራኤል ላይ የእግዚአብሔር ቁጣ ነደደ

ቁጣ የሚነድ እሳት ይመስል እግዚአብሔር እንደ ተቆጣ ተነግሯል። አ.ት፡ “እግዚአብሔር በእስራኤል ላይ በጣም ተቆጣ” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

በፍልስጥኤማውያንና በአሞናውያን እጅ ሸጣቸው

እግዚአብሔር ፍልስጥኤማያንና አሞናውያን እስራኤላውያንን እንዲያሸንፉ መፍቀዱ እስራኤላውያንን ለእነርሱ እንደሸጠላቸው ሆኖ ተነግሯል። (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

በ… እጅ

እዚህ ጋ “እጅ” የሚወክለው ኃይልን ወይም መቆጣጠርን ነው። (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)