ከእርሱ ጋር የነበሩት ሰዎች ሁሉ
“አቤሜሌክን የተከተሉ ሰዎች ሁሉ” ወይም “ለአቤሜሌክ ይዋጉ የነበሩ ሰዎች ሁሉ”
በሴኬም ላይ የሚያደፍጡትን አስቀመጡ
እዚህ ጋ “ሴኬም” የሚወክለው የሴኬምን ሰዎች ነው። አ.ት፡ “የሴኬምን ሰዎች በድንገት ለማጥቃት ተደበቁ” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
አራት ቦታ አካፍሎ
“በ4 ቡድኖች ለያይቶ” (ቁጥሮች የሚለውን ተመልከት)
ገዓል -- ኤቤድ
እነዚህን ስሞች በመሳፍንት 9፡26 ላይ እንዴት እንደተረጎምካቸው ተመልከት።