am_tn/jdg/09/28.md

2.5 KiB

ገዓል -- ኤቤድ

እነዚህን ስሞች በመሳፍንት 9፡26 ላይ እንዴት እንደተርጎምከው ተመልከት።

እንድናገለግለው አቤሜሌክ ማነው? ሴኬምስ ማነው?

ገዓል የሰኬም ሰዎች አቤሜሌክን ማገልገል እንደሌለባቸው አጽንዖት ለመስጠት ጥያቄ ይጠይቃል። አ.ት፡ “አቤሜሌክን ማገልገል የለብንም!” (ምላሽ የማይሻ ጥያቄ የሚለውን ተመልከት)

እንድናገለግለው አቤሜሌክ ማነው? ሴኬምስ ማነው?

እነዚህ ሁለቱም ጥያቄዎች አንድ ናቸው። የአቤሜሌክ እናት ከሴኬም በመሆኗ ምክንያት ገዓል አቤሜሌክን ለማመልከት “ሴኬም” ይላል። አ.ት፡ “አቤሜሌክን ማገልገል የለብንም፣ እርሱም ሴኬም ነው!” ( እና ምላሽ የማይሻ ጥያቄ የሚለውን ተመልከት)

እርሱ የይሩበአል ልጅ አይደለምን? ዜቡልስ የእርሱ ሹም አይደለምን?

ገዓል የሰኬም ሰዎች አቤሜሌክን ማገልገል እንደሌለባቸው አጽንዖት ለመስጠት ጥያቄ ይጠይቃል። አ.ት፡ “እርሱ የይሩበአል ልጅ ብቻ ነው፣ ዜቡልም የእርሱ ሹም ብቻ ነው” (ምላሽ የማይሻ ጥያቄ የሚለውን ተመልከት)

ይሩበአል

ይህ የጌዴዎን ሌላው ስሙ ነው። ይህንን በመሳፍንት 6፡32 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት።

ዜቡል

ይህ የሰው ስም ነው። (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)

የሴኬምን አባት የኤሞርን ሰዎች አገልግሉ

ገዓል የሚለው፣ የሴኬም ሰዎች ማገልገል ያለባቸው እውነተኛ ከነዓናውያን የሆኑትን ከኤሞር የተወለዱትን እንጂ እስራኤላዊ አባት ያለውን ሰው ማገልገል የለባቸውም።

አቤሜሌክን የምናገለግለው ለምንድነው?

ገዓል የሰኬም ሰዎች አቤሜሌክን ማገልገል እንደሌለባቸው አጽንዖት ለመስጠት ጥያቄ ይጠይቃል። አ.ት፡ “አቤሜሌክን ማገልገል የለብንም!” (ምላሽ የማይሻ ጥያቄ የሚለውን ተመልከት)

እነዚህ ሰዎች ከትዕዛዜ ስር እንዲሆኑ እመኛለሁ

“የሴኬምን ሰዎች ባስተዳድር እመኛለሁ”