am_tn/jdg/09/19.md

2.3 KiB

ከጌዴዎንና ከቤቱ ጋር በታማኝነትና በቅንነት አድርጋችሁ ከሆነ

ኢዮአታም ያደረጉት መልካም ይሆን እንደሆነ ምርጫውን ያቀርብላቸዋል፣ ይሁን እንጂ ያደረጉት በመሠረቱ መልካም እንደሆነ ኢዮአታም አያምንም። አ.ት፡ “ለይሩበአልና ለቤተሰቡ ሊደረግላቸው የሚገባቸውን አድርጋችሁላቸው ከሆነ”

ይሩበአል

ይህ የጌዴዎን ሌላው ስሙ ነው። እንዲህ ማለትም፣ “በኣል ለራሱ ይሟገት” ማለት ነው። ይህንን በ6፡32 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት።

ለቤቱ

እዚህ ጋ “ቤት” የሚያመለክተው ቤተሰብን ነው። አ.ት፡ “ቤተሰቡን” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

ካልሆነ ግን

ኢዮአታም ያደረጉት ክፉ መሆኑን እና እርግማን እንደሚሆንባቸው ተቃራኒውን አማራጭ ያቀርብላቸዋል። ኢዮአታም ያደረጉት ክፉ መሆኑን ያምናል። አ.ት፡ “ለይሩበአልና ለቤተሰቡ ሊደረግ የማይገባቸውን አድርጋችሁ ከሆነ ግን”

ከአቤሜሌክ እሳት ይውጣ፣ የሴኬምንም ሰዎች ያንድድ

ኢዮአታም የሚናገረው እርግማንን ነው። አቤሜሌክ በእሳት ያቃጥላቸው ይመስል የሴኬምን ሰዎች እንደሚያጠፋቸው ይናገራል። (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

አቤሜሌክን ለማንደድ እሳት ከሴኬምና ከቤትሚሎ ሰዎች ይውጣ

ኢዮአታም የሚናገረው እርግማንን ነው። የሴኬምና የቤትሚሎ ሰዎች በእሳት ያቃጥሉት ይመስል አቤሜሌክን እንደሚያጠፉት ይናገራል። (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

ቤትሚሎ

ይህ የቦታ ስም ነው። ይህንን በመሳፍንት 9፡6 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት።

ብኤር

ይህ የአንዲት ከተማ ስም ነው። (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)