am_tn/jdg/09/15.md

2.4 KiB

የእሾህ ቁጥቋጦው ለዛፎቹ እንዲህ አላቸው

በዚህ ምሳሌ ኢዮአታም የቁጥቋጦው እሾህና ዛፎቹ ሰዎች የሚያደርጓቸውን ነገሮች እንደሚያደርጉ ያብራራል። (ምሳሌዎች እና ሰውኛ የሚለውን ተመልከት)

በላያችሁ እንድነግሥ ልትቀቡኝ

አንድን ሰው በዘይት መቀባት ንጉሥ እንዲሆን የመሾም ምሳሌአዊ ድርጊት ነው። አ.ት፡ “ንጉሣችሁ አድርጋችሁ ልትቀቡኝ” (ምሳሌአዊ ድርጊት የሚለውን ተመልከት)

ደህንነት እንዲሆንላችሁ

“ደህንነት” የሚለው ቃል የነገር ስም ሲሆን እንደ ቅጽል ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “ተጠበቁ” (የነገር ስም የሚለውን ተመልከት)

እሳት ከእሾህ ቁጥቋጦው ይውጣ፣ የሊባኖስንም ዝግባዎች ያቃጥል

ይህ ማለት ዝግባዎቹን ለማቃጠል የእሾህ ቁጥቋጦው ይነዳል።

ከዚያም እሳት ከእሾህ ቁጥቋጦው ይውጣ

የእሾህ ቁጥቋጦው ራሱን እንደ “እሾህ ቁጥቋጦ” ያመለክታል። አ.ት፡ “ከዚያም እሳት ከእኔው ከእሾህ ቁጥቋጦው ይውጣ” (አንደኛ፣ ሁለተኛ ወይም ሦስተኛ መደብ የሚለውን ተመልከት)

አሁን

ይህ “በዚህ ሰዓት” ማለት አይደለም፣ ነገር ግን ትኩረትን ወደሚቀጥለው አስፈላጊ ጉዳይ ለመሳብ ጥቅም ላይ ውሏል።

ለይሩበአልና ለቤቱ መልካም አድርጋችሁ ከሆነና የሚገባውን ቅጣት ሰጥታችሁት ከሆነ

ኢዮአታም ያደረጉት መልካም ይሆን እንደሆነ ምርጫውን ያቀርብላቸዋል፤ ይሁን እንጂ ያደረጉት በመሠረቱ መልካም እንደሆነ ኢዮአታም አያምንም። አ.ት፡ “መልካም የሆነውን አድርጋችሁ ከሆነና ልጆቹን ሁሉ ትገድሉበት ዘንድ ለይሩበአል የሚገባው ከሆነ”

ይሩበአል

ይህ የጌዴዎን ሌላው ስሙ ነው። ይህንን በመሳፍንት 6፡32 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተምልከት።

ቤቱ

እዚህ ጋ “ቤት” የጌዴዎንን ቤተሰብ ይወክላል። (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)