am_tn/jdg/09/07.md

1.1 KiB

ለኢዮአታም ይህ በተነገረው ጊዜ

ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “አቤሜሌክ ወንድሞቹን መግደሉን ኢዮአታም በሰማ ጊዜ” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)

ገሪዛን ተራራ

ይህ ተራራ ነው። (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)

ዛፎች በላያቸው ላይ ንጉሥ ለማንገሥ ተሰበሰቡ። የወይራውን ዛፍ ‘በእኛ ላይ ንገሥ’ አሉት

ኢዮአታም ሰዎች የሚያደርጓቸውን ነገሮች በዛፎች በመመሰል ያብራራል። (ምሳሌዎች እና ሰውኛ የሚሉትን ተመልከት)

በላያቸው ላይ ንጉሥ ለመቀባት

እዚህ ጋ በዘይት መቀባት አንድን ሰው ንጉሥ እንዲሆን መሾምን የሚወክል ምሳሌአዊ ድርጊት ነው። አ.ት፡ “በሁላቸውም ላይ እንዲገዛ ንጉሥ ለመሾም”

በእኛ ላይ ንገሥ

“ንጉሣችን ሁን”