am_tn/jdg/08/27.md

2.7 KiB

ጌዴዎን በጉትቻዎቹ ኤፉድ ሠራ

“ጌዴዎን የወርቅ ጉትቻዎቹን ኤፉድ ለመስሪያነት ተጠቀመበት”

ዖፍራ

የከተማይቱን ስም በመሳፍንት 6፡11 እንዳደረግኸው ተርጉመው።

በዚያ እስራኤል ሁሉ አመነዘሩበት

ይህ አመንዝራነትን በሚመስል መልክ ሐሰተኛ አምላክን ስለ ማምለካቸው ይናገራል። አ.ት፡ “እስራኤላውያን በዚያ ኤፉዱን በማምለካቸው በእግዚአብሔር ላይ ኃጢአትን ሠሩ” ( ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

እስራኤል በሙሉ

እዚህ ጋ “በሙሉ” በጣም ብዙዎቹ ልብሱን ማምለካቸውን አጽንዖት ለመስጠት የተደረገ ግነት ነው። አ.ት፡ “በእስራኤል በጣም ብዙ ሰዎች ልብሱን አመለኩት” (ግነትና ጥቅል አስተያየት የሚለውን ተመልከት)

እርሱም ለጌዴዎንና በቤቱ ላሉት ወጥመድ ሆነባቸው

ይህ አደን የሚያድን ሰው የሚያጠምደው ወጥመድ ይመስል ጌዴዎንና ቤተሰቡ ኤፉዱን ሊያመልኩት እንደተፈተኑ ያሳያል። አ.ት፡ “ለጌዴዎንና ለቤተሰቡ ፈተና ሆነባቸው” ወይም “ጌዴዎንና ቤተሰቡ እርሱን በማምለክ ኃጢአትን ሠሩ” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

በቤቱ ላሉት

እዚህ ጋ “በቤቱ” የሚወክለው የጌዴዎንን ቤተሰብ ነው። አ.ት፡ “ለቤተሰቡ” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

ስለዚህ ምድያም ለእስራኤል ሕዝብ ተገዛላቸው

ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “ሰለዚህ እግዚአብሔር ምድያማውያን በእስራኤል ሕዝብ ፊት እንዲገዙ አደረጋቸው” ወይም “ስለዚህ እስራኤላውያን ምድያማውያንን እንዲያሸንፉ እረዳቸው” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)

ራሳቸውን ቀና አላደረጉም

ይህ የአነጋገር ዘይቤ ነው። አ.ት፡ “እንደገና እስራኤልን አላጠቁም” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)

ስለዚህ ምድሪቱ ዐርፋ ነበር

እዚህ ጋ “ምድሪቱ” የሚወክለው የእስራኤልን ሕዝብ ነው። አ.ት፡ “ስለዚህ እስራኤላውያን በሰላም ኖሩ” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

አርባ ዓመት

x