am_tn/jdg/08/26.md

1.1 KiB

1,700 ሰቅል ወርቅ

“አንድ ሺህ ሰባት መቶ ሰቅል ወርቅ”። ዘመናዊውን የመጠን መለኪያ መጠቀም የሚያስፈልግ ከሆነ ይህንን ማድረግ የሚያስችሉ ሁለት መንገዶች አሉ። አ.ት፡ “18.7 ኪ.ግ ወርቅ” ወይም “ወደ 20 ኪ.ግ የሚጠጋ ወርቅ” (ቁጥሮች እና የመጽሐፍ ቅዱስ ክብደት መለኪያ የሚሉትን ተመልከት)

ግማሽ ክብ ቅርጽ ያላቸው ጌጣ ጌጦች

ይህንን በመሳፍንት 8፡21 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት

በአንገት ጌጥ ላይ የሚንጠለጠሉ ድሪዎች

በአንገት ሀብል ወይም ክር ላይ የሚንጠለጠሉ ትናንሽ ጌጣጌጦች

የምድያም ነገሥታት ይለብሱት የነበረውን

ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “የምድያም ነገሥታት የለበሱት” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)