am_tn/jdg/08/06.md

1.6 KiB

የዛብሄልና የስልማና እጆች አሁን በእጅህ ውስጥ አሉ?

መሪዎቹ ጥያቄ የሚያቀርቡት እስራኤላውያኑ ዛብሄልንና ስልማናን ገና ያለመማረካቸውን አጽንዖት ለመስጠት ነው። አ.ት፡ “እስካሁን ዛብሄልና ስልማናን አልማረክኻቸውም” (ምላሽ የማይሻ ጥያቄ የሚለውን ተመልከት)

የዛብሄልና የስልማና እጆች

እዚህ ጋ “እጆች” የሚያመለክተው ሙሉ ሰውነትን ነው።

አሁን በእጅህ

እዚህ ጋ “እጅ” የሚወክለው ኃይልን ወይም መቆጣጠርን ነው። (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

ለሰራዊትህ እንጀራ የምንሰጠው ለምንድነው?

መሪዎቹ የሚጠይቁት ለእስራኤላውያኑ እንጀራ የሚሰጡበት ምንም ምክንያት እንደሌለ አጽንዖት ለመስጠት ነው። አ.ት፡ “ለሰራዊትህ እንጀራ የምንሰጥበትን አንዳች ምክንያት አላገኘንም” (ምላሽ የማይሻ ጥያቄ የሚለውን ተመልከት)

ቆዳችሁን በበረሃ እሾህና አሜከላ እተለትለዋለሁ

የዚህ መግለጫ ሙሉ ትርጉም በይበልጥ መብራራት ይችላል። አ.ት፡ “በበረሃ እሾህና አሜከላ ጅራፍ በመሥራት እገርፋችኋለሁ፣ እቆራርጣችኋለሁ”

እሾህና አሜከላ

ስል፣ በሐረግ ወይም ዛፍ ቅርንጫፍ ላይ ጫፉ የሾለና ሰውና እንስሳን ለመቁረጥ የሚችል