am_tn/jdg/07/02.md

2.1 KiB

በምድያማውያን ላይ ድል እንድሰጥህ

“ድል” የሚለው ቃል የነገር ስም ሲሆን እንደ ግሥ ወይም ቅጽል ሊተረጎም ይችላል። አ.ት፡ “ምድያማውያንን ታሸንፋቸው ዘንድ እንድፈቅድልህ” ወይም “በምድያማውያን ላይ ባለ ድል ላደርግህ” (የነገር ስም የሚለውን ተመልከት”

የገዛ ራሳችን ኃይል አድኖናል

እዚህ ጋ “ኃይል” የሚወክለው ሕዝቡን ራሳቸውን ነው። አ.ት፡ “ያለ እግዚአብሔር እርዳታ ራሳችንን አድነናል” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

አሁን

ይህ “በዚህ ሰዓት” ማለት አይደለም፣ ነገር ግን ትኩረትን ወደሚቀጥለው አስፈላጊ ጉዳይ ለመሳብ ጥቅም ላይ ውሏል።

በሕዝቡ ጆሮ ዐውጅ

እዚህ ጋ “ጆሮ” የሰውን ሁለንተና ያመለክታል። አ.ት፡ “ለሕዝቡ ዐውጅ”

ማንም የሚፈራ፣ ማንም የሚንቀጠቀጥ

ሁለቱም ሐረጎች ያላቸው ትርጉም አንድ ነው። (ተመሳሳይነት የሚለውን ተመልከት)

የሚንቀጠቀጥ

ይህ ቃል የሚገልጸው አንድ ሰው ከፍርሐት የተነሣ ሊቆጣጠረው በማይችለው ሁኔታ መንቀጥቀጡን ነው። አ.ት፡ “በፍርሐት የሚንቀጠቀጥ”

ይመለስ

ወዴት እንደሚሄድ ግልጽ ማድረግ ትችላለህ። አ.ት፡ “ወደ ቤቱ ይመለስ”

ገለዓድ ተራራ

ይህ በገለዓድ አውራጃ የሚገኝ ተራራ ስም ነው። (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)

ሃያ ሁለት ሺህ

“22,000” (ቁጥሮችን ተመልከት)

አሥር ሺህ ቀሩ

በውስጠ ታዋቂነት “ሰዎች” ወይም “ወንዶች” የሚል ቃል መኖሩን ይረዷል። አ.ት፡ “10,000 ሰዎች ቀሩ” ወይም “10,000 ወንዶች ቀሩ”

አሥር ሺህ

x