am_tn/jdg/06/13.md

1.8 KiB
Raw Permalink Blame History

ጌታዬ

ጌዴዎን “ጌታዬ” የሚለውን ቃል የሚጠቀመው እንግዳ የሆነን ሰው በትህትና ሰላምታ ለመስጠት ነው። እርሱ የሚናገረው በመልአክ ወይም በሰው መልክ ከታየው ከእግዚአብሔር ጋር እንደሆነ አልተገነዘበም።

‘እግዚአብሔር ከግብፅ ያወጣን አይደለምን? ብለው አባቶቻችን የነገሩን ተአምራቱ ሁሉ የት አለ?

እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር እንዳለ የነገረውን እንግዳ ለመገዳደር ጌዴዎን ጥያቄ ያቀርብለታል። ደግሞም፣ በቀጥታ የተጠቀሰው ትዕምርተ ጥቅስ ቀጥተኛ ባልሆነ ትዕምርተ ጥቅስ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “እግዚአብሔር አባቶቻችንን ከግብፅ ባወጣቸው ጊዜ ስላደረገላቸው የነገሩንን ዓይነት ተአምር አንድም አላየንም”። (ምላሽ የማይሻ ጥያቄ፣ ቀጥተኛ እና ቀጥተኛ ያልሆነ ትዕምርተ ጥቅስ የሚለውን ተመልከት)

በምድያማውያን እጅ ሰጥቶናል

“በ… ሰጥቶናል” የሚለው ሐረግ እስራኤላውያን እንዲሸነፉ እግዚአብሔር ፈቅዷል ማለት ነው። አ.ት፡ “ምድያማውያን እንዲያሸንፉን ፈቅዷል”

በ… እጅ ሰጥቶናል

እዚህ ጋ “እጅ” የሚወክለው ኃይልን ወይም ቁጥጥርን ነው። (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

በምድያም

እዚህ ጋ “ምድያም” የሚወክለው የምድያምን ሕዝብ ነው። አ.ት፡ “በምድያማውያን”(ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)