am_tn/jdg/06/05.md

1.5 KiB

እነርሱ ከከብቶቻቸውና ከድንኳኖቻቸው ጋር ወጥተው በሚመጡበት ጊዜ ሁሉ

የምድያም ምድር በቀይ ባህር አቅራቢያ ከእስራኤል ምድር በስተደቡብ ነበር። ከምድያም ወደ እስራኤል የሚደረግ ጉዞ በሚነገርበት ጊዜ “ወጥተው በሚመጡበት” የሚለውን ሐረግ መጠቀም የተለመደ ነበር። አ.ት፡ “ምድያማውያን ከብቶቻቸውንና ድንኳኖቻቸውን ወደ እስራኤል ምድር በሚያመጡበት ጊዜ ሁሉ”

እንደ አንበጣ መንጋ ይመጡ ነበር

ምድያማውያን እጅግ ብዙ ሆነው ይመጡ ስለነበርና ከብቶቻቸው የሚበቅለውን ነገር ሁሉ ይበሉት ስለነበር ከአንበጣ መንጋ ጋር ተነጻጽረዋል።

ለመቁጠር አይቻልም ነበር

ይህ ቁጥሩ በጣም ብዙ መሆኑን ለማሳየት የቀረበ ግነት ነው። (ግነት እና ጥቅል አስተያየት የሚለውን ተመልከት)

ምድያም አደከማቸው

እዚህ ጋ “ምድያም” የሚወክለው የምድያምን ሕዝብ ነው። (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

ወደ እግዚአብሔር ጮኹ

ይህ የአነጋገር ዘይቤ ነው። አ.ት፡ “እንዲረዳቸው ወደ እግዚአብሔር ጸለዩ” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)