1.2 KiB
1.2 KiB
በእግዚአብሔር ፊት ክፉ የሆነውን
የእግዚአብሔር ፊት የሚወክለው ፍርዱን ወይም ምዘናውን ነው። አ.ት፡ “በእግዚአብሔር ፍርድ ክፉ የሆነውን” ወይም “እግዚአብሔር ክፉ ነው ያለውን” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
የምድያማውያን እጅ
እዚህ ጋ “ምድያማውያን” የሚወክለው የምድያምን ሰዎች ነው። በተጨማሪም፣ “እጅ” መቆጣጠርን ይወክላል። አ.ት፡ “የምድያም ሰዎች መቆጣጠራቸው” ወይም “የምድያማውያን መቆጣጠር” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
የምድያም ኃይል እስራኤልን አስጨነቀ
እዚህ ጋ “የምድያም ኃይል” የሚያመለክተው የምድያም ሰዎችን ነው። አ.ት፡ “የምድያም ሰዎች ከእስራኤል ሰዎች ይልቅ እጅግ በርትተው ስለነበር አስጨነቋቸው” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
ዋሻ
ሊያስጠልል የሚችል በዐለታማ ሸንተረር ላይ የሚገኝ ስፍራ