am_tn/jdg/05/29.md

2.1 KiB

ጠቢብ ልዕልቶች

“ልዕልት” የንጉሥ ልጅ ናት፣ ነገር ግን “ልዕልቶች” ማለት ደግሞ ምናልባት የንጉሡን ቤተሰቦች የሚያማክሩ ሴት አማካሪዎች ማለት ሊሆን ይችላል። አ.ት፡ “ጠቢብ ሴቶች”

ለራሷ ተመሳሳይ ምላሽ ሰጠች

“ያንኑ ነገር ለራሷ ተናገረች”

ምርኮ አግኝተው ተከፋፍለው አልጨረሱ ይሆን?

ሴቶቹ በእርግጥ የሆነው ይኸው ነው ብለው ስላመኑበት ጉዳይ አጽንዖት ለመስጠት ጥያቄ ይጠቀማሉ። አ.ት፡ “ለመከፋፈል ጊዜ የፈጀባቸው ብዙ ምርኮ እግኝተው መሆን አለበት” (መልስ የማይሻ ጥያቄ የሚለውን ተመልከት)

ከበዘበዟቸው ላይ - አንድ ማህፀን፣ እያንዳንዱ ሁለት ማህፀን

ሴቶቹ በእርግጥ የሆነው ይኸው ነው ብለው ስላመኑበት ጉዳይ አጽንዖት ለመስጠት ጥያቄ ይጠቀማሉ። አ.ት፡ “ከበዘበዟቸው ላይ ለእያንዳንዱ ወንድ አንድ ማህፀን፣ ሁለት ማህፀን ደርሷቸው መሆን አለበት” (መልስ የማይሻ ጥያቄ የሚለውን ተመልከት)

ለእያንዳንዱ ወንድ አንድ ማህፀን፣ ሁለት ማህፀን

እዚህ ጋ “ማህፀን” የሚያመለክተው ሴትን ነው። የሲሣራ ሰዎች ብዙ ሴቶችን እንደማረኩ የሲሣራ እናት ታምናለች። አ.ት፡ “እያንዳንዱ ወታደር አንድ ወይም ሁለት ሴት ይደርሰዋል”

የቀለመ ጨርቅ

“ልዩ ልዩ ቀለም ያለው ልብስ” ወይም “ልዩ ልዩ ቀለም ያላቸው ልብሶች”

ማቅለም

ልዩ ልዩ ቀለማት ካላቸው ክሮች የተሠሩ ንድፎች

ለሚበዘብዙት ለአንገታቸው

እዚህ ጋ “አንገታቸው” የሚወክለው የሲሣራን ወታደሮች ነው። አ.ት፡ “የበዘበዙት ወታደሮች ሊለብሱት”