am_tn/jdg/05/26.md

1.3 KiB

እጇን ወደ ድንኳኑ ካስማ ሰደደች

“ኢያዔል በግራ እጇ የድንኳኑን ካስማ ያዘች”

የድንኳን ካስማ

ይህ ድንኳኑን ከመሬት ጋር አገናኝቶ እንዲይዝ በመዶሻ የሚመታ እንደ ትልቅ ሚስማር የሾለ እንጨት ወይም ብረት ነው። ይህንን በመሳፍንት 4፡21 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት።

ቀኝ እጇን ሠራተኛ ወደሚጠቀምበት መዶሻ

ይህ ሙሉ ዐረፍተ ነገር ሆኖ መነገር ይችላል። አ.ት፡ “በቀኝ እጇ መዶሻ ያዘች”

መዶሻ

የድንኳኑን ካስማ ወደ መሬት ለማጥለቅ ክብደት ካለው እንጨት የሚሠራ መምቻ ነው። ይህንን በመሳፍንት 4፡21 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት።

ሲሣራ

የዚህን ሰውዬ ስም በመሳፍንት 4፡2 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት፡

መዛል

ዐቅም ማጣት ወይም መንቀሳቀስ አለመቻል

በቁጣ ተገደለ

ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “ገደለችው” ወይም “ሞተ”(አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)