am_tn/jdg/05/19.md

1.9 KiB

ነገሥታት መጡ፣ ተዋጉም - የከነዓን ነገሥታት ተዋጉ

ራሱንና የሚያዛቸውን ሰራዊት ለማመልከት የአንድ ሕዝብ ወገን ንጉሥ የሚለው ጥቅም ላይ ውሏል። አ.ት፡ “ነገሥታትና ሰራዊቶቻቸው መጥተው ተዋጉ - የከነዓን ነገሥታትና ሰራዊቶቻቸው ተዋጉ”

እነርሱ ተዋጉ -- ተዋጉ

“እኛ” የሚለው ቃል የሚታወቅ ነው። አ.ት፡ “ወጉን - ወጉን”

ታዕናክ - መጊዶ

የእነዚህን ቦታዎች ስም በመሳፍንት 1፡27 እንዳደረግኸው ተርጉማቸው።

ምንም ብር አልበዘበዙም

እዚህ ጋ “ብር” በጥቅሉ የትኛውንም ዓይነት ገንዘብ ይወክላል። አ.ት፡ “የሚበዘብዙት ብር ወይም ሌላ ሀብት አልነበረም”

ብዝበዛ

አብዛኛውን ጊዜ በጦርነት ወይም በሌቦች አማካይነት በማስገደድ የሚወሰዱ ነገሮች

ከዋክብት ከሰማይ ተዋጉ፣ ከሰማያት ጥጎቻቸው ሲሣራን ተዋጉት

እግዚአብሔር፣ እስራኤላውያን ሲሣራንና ሰራዊቱን ድል እንዲያደርጓቸው መርዳቱ ከዋክብት ራሳቸው ሲሣራንና ሰራዊቱን እንደተዋጓቸው ተደርጎ ተነግሯል። ይህ እግዚአብሔር ሲሣራን ድል ለማድረግ ተፈጥሮአዊ ግብዓቶችን በተለይም ነጎድጓድን መጠቀሙን ያመለክት ይሆናል። (ሰውኛ የሚለውን ተመልከት)

በሲሣራ ላይ

እዚህ ጋ “ሲሣራ” የሚወክለው ራሱንና መላውን ሰራዊቱን ነው። አ.ት፡ “ሲሣራና ሰራዊቱ”

ሲሣራ

ይህንን ስም በመሳፍንት 4፡2 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት።