am_tn/jdg/05/15.md

1.7 KiB

በይሳኮር ያሉ መስፍኖቼ ከዲቦራ ጋር ነበሩ

እዚህ ጋ “የእኔ” የሚያመለክተው ዲቦራን ነው። ይህ መግለጫ በአጠቃላይ በአንደኛ መደብ ሊተረጎም ይችላል። አ.ት፡ “በይሳኮር የሚገኙት መስፍኖቼ ከእኔ ጋር ነበሩ” (አንደኛ፣ ሁለተኛ፣ ወይም ሦስተኛ መደብ የሚለውን ተመልከት)

ዲቦራ

ይህንን ስም በመሳፍንት 4፡4 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት

ይሳኮር ከባርቅ ጋር ነበር

እዚህ ጋ “ይሳኮር” የይሳኮርን ነገድ ያመለክታል። አ.ት፡ “የይሳኮር ነገድ ከባርቅ ጋር ነበር” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

ባርቅ

ይህንን ስም በመሳፍንት 4፡6 እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት።

መመሪያውን በመከተል ከበስተኋላው ወደ ሸለቆው ሮጡ

“መመሪያውን በመታዘዝና ወደ ሸለቆው ከበስተኋላው በመሮጥ”

ከበስተኋላው በመሮጥ

“ከኋላው በመከተል” ወይም “ከኋላው በመሮጥ”

ታላቅ የልብ ምርምር ነበር

እዚህ ጋ “ልብ” አሳብን ይወክላል። የሰዎቹ እርስ በእርስ መነጋገርና ምን ማድረግ እንዳለባቸው መወሰን አለመቻላቸው ልባቸውን እንደመረመሩ ተደርጎ ተነግሯል። አ.ት፡ “ምን ማድረግ እንዳለባቸው ብዙ ውይይት ነበር” (ፈሊጣዊ እና ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)