am_tn/jdg/05/09.md

1.1 KiB

ልቤ ወደ እስራኤል አዛዦች ይሄዳል

“ልብ” የሚለው ቃል የአንድን ሰው ስሜት ይወክላል። “ልቤ ይሄዳል” የሚለው ሐረግ ዲቦራ ያላትን አድናቆት ወይም ምስጋና የማመልከቻ መንገድ ነው። አ.ት፡ “የእስራኤልን አዛዦች አደንቃለሁ” (ፈሊጣዊ አነጋገር እና የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)

እናንተ በነጫጭ አህዮች የምትቀመጡ - በመንገዱ ላይ የምትሄዱ

ይህ ንጽጽር የሚያመለክተው ምናልባት ባለጸጎችንና ድኾችን ይሆናል። አ.ት፡ “እናንት በነጫጭ አህዮች የምትቀመጡ ባለጸጎች … እናንት በመንገዱ ላይ የምትሄዱ ድኾች”

ለኮርቻ በስጋጃዎች ላይ ተቀምጣችሁ

እነዚህ ስጋጃዎች ምናልባት ጋላቢው በይበልጥ እንዲመቸው በአህያው ጀርባ ላይ ለኮርቻነት የሚጠቀምባቸው ሳይሆኑ አይቀሩም።