am_tn/jdg/05/05.md

1.8 KiB

ተራሮች ተንቀጠቀጡ

ይህ እግዚአብሔርን በጣም በመፍራታቸው ተራሮች መንቀጥቀጣቸውን ለማሳየት፣ ምናልባት የምድር መናወጥን ያመለክት ይሆናል። አ.ት፡ “ተራሮች በፍርሃት ተርበደበዱ”

በእግዚአብሔር ፊት

እዚህ ጋ “ፊት” የእግዚአብሔርን ሀልዎት ያመለክታል። አ.ት፡ “በእግዚአብሔር ሀልዎት ፊት” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

የሲና ተራራ እንኳን ተንቀጠቀጠ

ሙሴና እስራኤል በሲና ተራራ በነበሩ ጊዜ ተንቀጥቅጦ ነበር። አ.ት፡ “ከዓመታት በፊት የሲና ተራራ እንኳን ተንቀጥቅጧል”

በ… ቀናት

“በ… የሕይወት ዘመን”

ሰሜጋር = ዓናት = ኢያዔል

እነዚህ የሰዎች ስሞች ናቸው። ሰሜጋርና ዓናትን በመሳፍንት 3፡31 ላይ እንዲሁም ኢያዔልን በመሳፍንት 4፡18 ላይ እንዴት እንደተረጎምካቸው ተመልከት። (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)

የዓናት ልጅ

ሰሜጋርንና የኖረበትን ዘመን መለየት እንዲቻል ለመርዳት የሰሜጋር አባት ተጠቅሷል። (ዳራዊ መረጃ የሚለውን ተመልከት)

አውራ ጎዳናዎቹ ተትተዋል

ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር የሚችል ሲሆን መንገዶቹ የተተዉበትን ምክንያት ግልጽ ማድረግ ትችላለህ። አ.ት፡ “የእስራኤልን ጠላቶች ስለ ፈሩ ሰዎች አውራ ጎዳናዎቹን መጠቀም አቆሙ” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ፣ የሚለውን ተመልከት)