am_tn/jdg/02/20.md

2.4 KiB

የእግዚአብሔር ቁጣ በእስራኤል ላይ ነደደ

የእግዚአብሔር ቁጣ እንደ እሳት እንደ ነደደ ተገልጿል። ይህንን በመሳፍንት 2፡14 ላይ እንዴት እንደ ተረጎምከው ተመልከት።

ይህ ሕዝብ ተላልፏል

እዚህ ጋ “ሕዝብ” የሚወክለው ሰዎቹን ነው። አ.ት፡ “እነዚህ ሰዎች ተላልፈዋል” ወይም “እስራኤላውያኑ ተላልፈዋል” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

አባቶች

እዚህ ጋ፣ ይህ የሚያመለክተው የአንድ ሰው ወይም የአንድ ሕዝብ ወገን የሆኑ አያቶችን ነው።

እነርሱ ድምፄን አልሰሙም

እዚህ ጋ “ድምፅ” የሚወክለው እግዚአብሔር የተናገረውን ነው። አ.ት፡ “እኔ ያዘዝኳቸውን አልታዘዙም” ወይም “አልታዘዙኝም”(ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

የትኞቹም ሕዝቦች

እዚህ ጋ “ሕዝቦች” የሚለው ቃል የሚያመለክተው ከእስራኤል በፊት በከነዓን ይኖሩ የነበሩትን የሕዝብ ወገን ነው። (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

እነርሱ የእግዚአብሔርን መንገድ ይጠብቃሉ፣ ይሄዱበታልም

ሰዎች እንዲኖሩት ወይም እንዲያደርጉት እግዚአብሔር የሚፈልገው ሕይወት እንደ መንገድ ወይም ጎዳና ተደርጎ ተነግሯል። እግዚአብሔርን የሚታዘዝ ሰው በመንገዱ ላይ እየሄደ እንዳለ ተነግሯል። (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

ፈጥኖ አስወጥቶ በኢያሱ እጅ አልሰጣቸውም

እነዚህ ሁለት ሐረጎች የሚሉት አንድ ነገር ስለሆነ መጣመር ይችላሉ። አ.ት፡ “ኢያሱ ፈጥኖ እንዲያሸንፋቸውና እንዲያስወጣቸው አላደረገም”

በኢያሱ እጅ

እዚህ ጋ “እጅ” ኃይልን የሚገልጽ ፈሊጣዊ አነጋገር ሲሆን “ኢያሱ” ራሱንና ሰራዊቱን ይወክላል። አ.ት፡ “በኢያሱና በሰራዊቱ ኃይል ሥር” (ፈሊጣዊ አነጋገር እና የሚለውን ተመልከት)