am_tn/jdg/02/18.md

2.4 KiB

እግዚአብሔር መሳፍንትን ባስነሣላቸው ጊዜ

እግዚአብሔር እንዲፈርዱ ሰዎችን መሾሙ ሰዎችን እንዳነሣቸው ወይም ብድግ እንዳደረጋቸው ተደርጎ ተነግሯል። (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

መሳፍንትን ለእነርሱ … አዳኑአቸው

“እነርሱ” የሚለው ቃል እስራኤላውያንን ያመለክታል።

የጠላቶቻቸው እጅ

እዚህ ጋ “እጅ” እስራኤልን የሚጎዱበትን የጠላትን ኃይል ያመለክታል። አ.ት፡ “የጠላቶቻቸውን ኃይል” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

መስፍኑ በኖረበት ዘመን ሁሉ

“መስፍኑ በሕይወት እስከ ኖረ ድረስ”

ማዘን

ለአንድ ሰው ወይም ለአንድ ነገር የርኅራኄ መኖር

በጮኹ ጊዜ

አንድ ሰው ከመከራው የተነሣ የሚጮኸው ጩኸት፣ እስራኤላውያኑ በመከራቸው ጊዜ ስቃያቸውን ለመግለጽ ጥቅም ላይ ውሏል። አ.ት፡ “በተሠቃዩ ጊዜ” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

ተመለሱ

ሕዝቡ ለእግዚአብሔር ከቶ ያለመታዘዛቸው በአካል ከእግዚአብሔር እንደ ተለዩ ተደርጎ ተነግሯል። (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

አባቶቻቸው

“ቅድመ አያቶቻቸው” ወይም “የቀድሞ አባቶቻቸው”

ሄደው ሌሎች አማልክቶችን አገለገሉ፣ አመለኳቸውም

የእስራኤላውያን ሌሎች አማልክትን ማምለክ ከሌሎች አማልክት ኋላ እየተራመዱ እንደሄዱ ተደርጎ ተነግሯል። አ.ት፡ “ሌሎች አማልክትን አገለገሉ፣ ሰገዱላቸውም” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

የትኛውንም ክፉ ሥራቸውን ወይም የእልኸኝነት መንገድ ለመተው እምቢ አሉ

“ክፉ ነገር ማድረጋቸውንና እልኸኛ መሆናቸውን ለማቆም እምቢ አሉ”። ይህ በአዎንታዊ አገላለጽ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “ክፉ ነገር ማድረጋቸውንና እልኸኝነታቸውን ቀጠሉ”