am_tn/jdg/02/14.md

3.2 KiB

የእግዚአብሔር ቁጣ በእስራኤል ላይ ነደደ

የእግዚአብሔር ቁጣ እንደ እሳት እንደሚቃጠል ተገልጿል። አ.ት፡ “እግዚአብሔር በእስራኤል ሕዝብ ላይ በጣም ተቆጣ” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

ሀብታቸውን ለሚቀሟቸው ለወራሪዎች አሳልፎ ሰጣቸው

“ወራሪዎች ሀብታቸውን እንዲቀሟቸው ተዋቸው”

ከእንግዲህ ራሳቸውን ከጠላቶቻቸው መከላከል እንዳይችሉ፣ በዙሪያቸው ለተገዙላቸው ጠላቶቻቸው እንደ ባሪያ ሸጣቸው።

ጠላቶች እስራኤላውያኑን እንደ ባሪያ አድርገው እንዲወስዷቸው እግዚአብሔር መፍቀዱ ለባርነት ሸጣቸው ተብሎ ተነግሯል። “ለተገዙላቸው” የሚለው ቃል በአድራጊ ድምፅ ሊተረጎም ይችላል። አ.ት፡ “እርሱ፣ ጠላቶቻቸው ድል እንዲያደርጓቸውና ባሪያ አድርገው እንዲወስዷቸው፣ ከእንግዲህም ብርቱዎቹን ጠላቶቻቸውን መቋቋም እንዳይችሉ ፈቀደ”። (ዘይቤአዊ አነጋገር፣ አድራጊና ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)

ይሸነፉ ዘንድ የእግዚአብሔር እጅ በእነርሱ ላይ ነበረች

እዚህ ጋ “እጅ” የሚወክለው የእግዚአብሔርን እጅ ነው። አ.ት፡ “ያሸንፏቸው ዘንድ እግዚአብሔር ጠላቶቻቸውን ረዳቸው” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

እጅግ ተጨንቀው ነበር

“እጅግ ተሠቃይተው ነበር”

ከዚያም እግዚአብሔር መሳፍንትን አስነሣላቸው

እግዚአብሔር እንዲፈርዱ ሰዎችን መሾሙ ሰዎችን እንዳነሣቸው ወይም ብድግ እንዳደረጋቸው ተደርጎ ተነግሯል። (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

ከእነዚያ እጅ

እዚህ ጋ “እጅ” የሚያመለክተው ኃይልን ነው። አ.ት፡ “ከጠላቶቻቸው ኃይል” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

መሳፍንታቸውን አልሰሙም

“መሳፍንታቸውን አልታዘዙም”

ራሳቸውን እንደ ሴተኛ አዳሪዎች ለሌሎች አማልክት ሰጡ፣ አመለኳቸውም

የሕዝቡ እግዚአብሔርን ከድቶ ሌሎች አማልክትን ማምለክ እንደ ሴተኛ አዳሪ እንዲቆጠሩ ማስደረጉ ተነግሯል። አ.ት፡ “ሐሰተኛ አማልክትን በማምለክ ከዱት”

አባቶቻቸው ከኖሩበት መንገድ ፈጥነው ተመለሱ

ሕዝቡ እግዚአብሔርን እንዳመለኩ እንደ ቀድሞ አባቶቻቸው ያለማድረጋቸው፣ ከአባቶቻቸው መንገድ ተመልሰው በሌላ አቅጣጫ እንደሄዱ እንዲነገርላቸው ሆኗል። (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

አባቶቻቸው

“ቅድመ አያቶቻቸው” ወይም “የቀድሞ አባቶቻቸው”