am_tn/jdg/02/06.md

1.9 KiB

አሁን ኢያሱ በ … ጊዜ

እዚህ ጋ “አሁን” የሚለው ቃል ጥቅም ላይ የዋለው ዋነኛው ታሪክ የተገታበትን ለመለየት ነው። እዚህ ላይ ከኢያሱ በኋላ የነበረው ትውልድ እንዴት ኃጢአትን እንደ ሠሩና ሐሰተኞች አማልክትን እንዳመለኩ፣ እግዚአብሔር እንደቀጣቸው ሆኖም እንዲታደጓቸው መሳፍንትን እንደላከላቸው ተራኪው ጠቅለል ያለ ማብራሪያ መስጠት ይጀምራል። ይህ ማጠቃለያ የሚያበቃው በ2፡23 ላይ ነው።

ኢያሱ 110 ዓመት ሆኖት በሞተ ጊዜ

በ1፡1-2፡5 ላይ ያለው ሁነት የተፈጸመው ከኢያሱ ሞት በኋላ ነው። ይህ በኢያሱ መጽሐፍ መጨረሻ የተፈጸሙት ሁነቶች በድጋሚ የታሰቡበት ነው።

ወደ ተመደበላቸው ስፍራ

ይህ አገላለጽ በይበልጥ ግልጽ መሆን ይችላል። አ.ት፡ “ እግዚአብሔር ወደ ሰጣቸው ስፍራ”

በሕይወት ዘመኑ

ይህ ማለት አንድ ሰው የኖረበት ጊዜ ማለት ነው። አ.ት፡ “ዕድሜውን ሙሉ”

ሽማግሌዎች

ይህ ማለት የሙሴን ሕግ ከማስጠበቅ አንጻር በማኅበራዊ ፍትሕና ሀይማኖታዊ ጉዳዮች ላይ እስራኤላውያንን ሲረዱ የነበሩ ሰዎች ናቸው።

ከእርሱ የበለጠ ኖረዋል

ይህ ማለት ከሌላው የበለጠ ዓመት መኖር ነው። አ.ት፡ “እርሱ ከኖረው የበለጠ ኖረዋል”

ነዌ

ይህ የአንድ ሰው ስም ነው። (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)

110 ዓመት ዕድሜው ላይ

“አንድ መቶ አሥር ዓመት ዕድሜው ላይ” (ቁጥሮች የሚለውን ተመልከት)