am_tn/jdg/02/03.md

1.4 KiB

አሁን እናገራለሁ፣ ‘…ወጥመድ አልሆንባችሁም’

ይህ በትዕምርተ ጥቅስ ውስጥ ያለ ትዕምርተ ጥቅስ ነው። ይህ ቀጥታ የሆነ ትዕምርተ ጥቅስ ቀጥተኛ እንዳልሆነ ተቆጥሮ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “…ወጥመድ እንደማልሆንባችሁ አሁን እነግራችኋለሁ”

ለጎናችሁ እሾህ ይሆናሉ

ከነዓናውያን እስራኤላውያንን ማስቸገራቸው ለእስራኤላውያን የጎን ውጋት እንደሚሆኑባቸው ተነግሯል። አ.ት፡ “መከራ ያመጡባችኋል” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

እሾኽ

እስከ 7 ሴንቲ ሜትር የሚረዝምና ከአንዳንድ እጽዋት ጋር አብሮ የሚበቅል ትናንሽ የሚወጉ ነገሮች ያሉበት እንጨት

አማልክቶቻቸው ወጥመድ ይሆኑባችኋል

እስራኤላውያኑ የከነዓናውያንን አማልክት ማምለካቸው ልክ አደን የሚያድን ሰው ያጠመደው ወጥመድ እንስሳውን ይዞ ለሞት እንደሚዳርገው ሁሉ ሐሰተኞቹ አማልክት አጥፊዎቻቸው እንደሚሆኑ ተነግሯል። (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

ጮኹና አለቀሱ

“በብዙ ዕንባ አለቀሱ”