am_tn/jdg/02/01.md

2.0 KiB

የእግዚአብሔር መልአክ

ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች 1) “እግዚአብሔርን የሚወክል መልአክ” ወይም 2) “እግዚአብሔርን የሚያገለግል መልዕከተኛ” ወይም 3) መልአክ መስሎ ከሰው ጋር የተነጋገረውን እግዚአብሔርን ራሱን ያመለክት ይሆናል የሚሉት ናቸው።

ከጌልገላ ወደ ቦኪም ወጣ

“ጌልገላን ትቶ ወደ ቦኪም ሄደ”

ቦኪም

መልአኩ ሕዝቡን ከገሰጻቸው በኋላ እስራኤላውያን ለዚህ ስፍራ በ2፡5 ላይ የሰጡት ስም ይህ ነው። “ቦኪም” ማለት “ማልቀስ” ማለት ነው። (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)

አላቸው

የእግዚአብሔር መልአክ ለእስራኤል ሕዝብ መናገሩ ግልጽ ነው።

ከግብፅ አወጣችሁ

“ከግብፅ መራችሁ”

አባቶቻችሁ

“ቅድም አያቶቻችሁ” ወይም “የቀድሞ አባቶቻችሁ”

ከእናንተ ጋር የገባሁትን ቃል ኪዳኔን አፈረሱ

ይህ ፈሊጣዊ አነጋገር ነው። አ.ት፡ “አደርግላችኋለሁ ያልሁትን እንዳላደርግ” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)

ድምፄን አልሰማችሁም

“ድምፅ” እዚህ ጋ የሚወክለው እግዚአብሔር የተናገረውን ነው። አ.ት፡ “ትዕዛዞቼን አልጠበቃችሁም” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

ይህ ያደረጋችሁት ምንድነው?

ይህ ጥያቄ የተጠየቀው የእስራኤል ሕዝብ እግዚአብሔርን እንዳልታዘዙና በዚህም ምክንያት መከራ እንደሚደርስባቸው እንዲገነዘቡ ነው። አ.ት፡ “የከፋ ነገር አድርጋችኋል” (መልስ የማይሻ ጥያቄ የሚለውን ተመልከት)