am_tn/jas/04/04.md

2.1 KiB

ያዕቆብ 4፡ 4-5

እናንተ አመንዝሮች! ይህ እግዚአብሔርን የማይታዘዙ ሰዎችን ከባሏ ውጪ ከሌላ ሰው ጋር የሚትተኛ ምስትን ያነጻጽራል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡ "እናንተ ከእግዚአብሔር ታማኞች አልሆናችሁም!" (ተመልከት: [[rc:///ta/man/translate/figs-metaphor]]) አታውቁምን . . . እግዚአብሔር? ያዕቆብ ተደራሲያኑን ለማስተማር ይህንን ጥያቄ ተጠቅሟል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡ "እናንተ ታውቃላችሁ . . . እግዚአብሔር!" (ተመልከት: [[rc:///ta/man/translate/figs-rquestion]]) ከዓለም ጋር ወዳጅነት “ከዓለም ጋር ወዳጅነት” የሚለው ሀረግ ከዓለም እሴት ሥርዓት እና ባሕርይ ጋር ራስን ማመሳሰል ወይም መሳተፍ የሚያመለክት ነው፡፡ (ተመልከት: [[rc:///ta/man/translate/figs-metonymy]]). ከዓለም ጋር መወዳጀት ከእግዚብሔር ጋር መጣላት ነው የዓለም እሴት ሥርዓት አካል መሆን የእግዚአብሔር ጠላት መሆን ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡ "እግዚአብሔር እንደማያከብሩ ሰዎች መኖር ልክ እግዚአብሔር እንደሚቃወም ሰው ነው፡፡" (ተመልከት: [[rc:///ta/man/translate/figs-metonymy]]) ወይም ቅዱሳት መጻሕፍት ያለ ትርጉም ይመስሏችኋልን ያዕቆብ ተደራሲያኑን ለማረታታት ጥያቄን ይጠቀማል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡ "ቅዱሳት መጻሕፍት እውነት ነው፡፡" እርሱ በውስጣችን ያስቀመጠው መንፈስ አንዳንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉሞች የሰው መንፈስን ለማመልከት “መንፈስ” ተጠቅመዋል፡፡ ቅዱሳት መጽሐፍት ውስጥ ቃሉ ያለው ትርጉም ይህም ሊሆን ይችላል፡፡ አንባቢያኑ የሚጠቀሟቸው ሌሎች ትርጉሞች ላይ ያለውን ቃል በትርጉምህ ውስጥ ተጠቀም፡፡