am_tn/jas/04/01.md

4.3 KiB

ያዕቆብ 4፡ 1-3

አያያዥ ዓረፍተ ነገር: ያዕቆብ እነዚህ አማኞችን ስለ ዓለማዊነታቸው እና ትህትና ማጣታቸው ይገስጽጻቸዋል፤ አንደበታቸውን ይጠብቁ እና እርስ በእርሳቸው በጥንቃቄ መነጋገር እንዳለባቸው ያበረታታቸዋል፡፡ አጠቃላይ መረጃ: በዚህ ክፍል ውስጥ “እራሳችሁ” የሚለው ቃል ውስጥ “እናንተ” እና እናንተ” የሚለው ቃል የብዙ ቁጥር አመልካች ቃል ሲሆን የሚያመለክተው ያዕቆብ የጻፈላቸውን አማኞችን ነው፡፡ በእናንተ ዘንድ ጦርና ጠብ ከወዴት ይመጣሉ? ያዕቆብ ተደራሲያንኑን ለማስተማር እና ለመገሰጽ ጥያቄን ተጠቅሟል፡፡ አማራጭ ትርጉም "እርስ በእርሳችሁ ሁል ጊዜ ለምን እንደሚትጣሉ አውቃለሁ፡፡" (ተመልከት: [[rc:///ta/man/translate/figs-rquestion]]) ጠብ እና ክርክር “ጠብ” እና “ክርክር” የሚለው ቃል በመሠረታዊ ትርጉሙ ተመሳሳይ ነው፡፡ ያዕቆብ እነዚህ ሁለት ቃላትን በአንድነት የተጠቀመበት ምክንያት በሰዎች መካከል ያለውን ማንኛውንም አይነት ጠብ ለማመልከት ነው፡፡ (ተመልከት: [[rc:///ta/man/translate/figs-doublet]]) በብልቶቻችሁ ውስጥ ከሚዋጉ ከእነዚህ ክፉ ምኞቶቻችሁ አይደሉምን? ያዕቆብ ይህንን ጥያቄ በዚህ ውስጥ የተጠቀመው ተደራሲያኑን ለመገሰጽ ነው፡፡ በእናንተ ቋንቋ ውስጥ አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ በዓረፍተ ነገር ቅርጽ ልጻፍ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡ "ከክፉ ምኞቶቻችሁ ውስጥ ይወጣሉ" ወይም "ከክፉ ምኞቶቻችሁ ስለምነሱ ነው፡፡" (ተመልከት: [[rc:///ta/man/translate/figs-rquestion]]) ከሚዋጉ ከእነዚህ ክፉ ምኞቶቻችሁ ያዕቆብ “ክፉ ምኞትን” በሰውኛ መልኩ በመግለጽ አማኞችን በመቃወም የሚዋጋ ወታደር አድርጎ ያቀረበዋል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡ “የሚትፈልጉት ክፋት ነው፣ ስለ ሌሎች አማኞች ፍላጎት ግድ አይላችሁም፡፡” (ተመልከት: [[rc:///ta/man/translate/figs-personification]]) በአማኞች ወዳጆቻችሁ መካከል? "በአካሎቻችሁ፡፡" አማራጭ ትርጉም 1) በአጥቢያ ቤተ ክርስቲያናት ውስጥ በሚገኙ ምዕመናን መካከል ጥል አለ፣ አማራጭ 2) ጥሉ ውስጣዊ ነው ማለትም ክፉ እና መልካም ነገርን በማድረግ መካከል፡፡ ያልለህን ነገር ትመኛለህ "ሁል ጊዜ የሚትፈልገው ያሌለህን ነገር ነው፡፡" ትገድላለህ፣ በብርቱም ትፈልጋለህ በዚህ ክፍል ውስጥ “ትገድላለህ” የሚለው ቃል የሚያመለክተው ሰዎች የሚፈልጉትን ነገር ለማግኘት እንዴት በከፋ ሁኔታ እንደሚሄዱ ያመለክታል፡፡ ይህ እንዲህ ተብሎ ሊተረጎም ይችላል “ማግኘት የማትችሉትን ለማግኘት ስትሉ ሁሉንም ዓይነት ክፋቶችን ታደርጋላችሁ፡፡” (ተመልከት: [[rc:///ta/man/translate/figs-hyperbole]]) ትጣላላችሁ እንዲሁም ትዋጉማላችሁ “መጣላት” እና “መዋጋት” የሚሉት ቃላት በመሠረታዊ ትርጉማቸው ተመሳሳይ ናቸው፡፡ እነዚህ ቃላት ያዕቆብ የተጠቀማቸው ሰዎች እርስ በእርሳቸው ምን ያኸል እንደሚከራከሩ አጽኖት ሰጥተው ለማሳየት ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡ "ሁል ጊዜ ትጣላላችሁ፡፡" (ተመልከት: [[rc:///ta/man/translate/figs-doublet]]) መጥፎ የሆኑ ነገሮችን ትለምናላችሁ "በመጥፎ ትጠይቃላችሁ፡፡" አማራጭ ትርጉም 1) "በተሳሳተ መነሻ ሀሳብ ትጠይቃላችሁ፣ አመለካካታችሁ መጥፎ ነው፡፡" ወይም 2) "ለተሳሳተ ዓላማ ወይም መጥፎ የሆኑ ነገሮችን ትጠይቃላችሁ፡፡" ታጠፉታላችሁ "ታጠፏቸዋላችሁ"