am_tn/jas/02/18.md

1.8 KiB

ያዕቆብ 2፡ 18-20

ይሁን እንጂ አንድ ሰው እንዲህ ይላል ያዕቆብ በ2፡ 14-17 ላይ አንድ የእርሱን ትምህርት የሚቃወም ሰውን በምናቡ እየሳለ ምን ልል እንደሚችል ይናገራል፡፡ ያዕቆብ ይህንን ሰው "ሞኝ ሰው" በማለት በቁጥር 20 ይጠራዋል፡፡ የዚህ ምናባዊ ገለጻ ዋና ዓላማ በተደራሲያኑ ዘንድ ያለው ስለ እምነት እና ሥራ ያለውን አመለካከት ለማስተካከል ነው፡፡ (ተመልከት: [[rc:///ta/man/translate/figs-hypo]]) እኔ ሥራ አለኝ እንዲሁም እኔ ሥራ አለኝ ያዕቀብ በእርሱ አስተምህሮ ዙሪያ አንዳንድ ሰዎች ሊያነሱ የሚችሉትን ተቃውሞ ይገልጻል፡፡ አማራጭ ትርጉም: "አንድ ሰው እምነት ካለው ይህ ተቀባይነት አለው እንዲሁም አንድ ሰው መልካም ሥራ ካለውም እንደዚያው፡፡" እምነትህን አሳየኝ በዚህ ሥፍራ ላይ “እኔ” የሚለው ቃል የሚያመለክተው ያዕቆብን ነው፡፡ ዳብሎስም . . . ይንቀጠቀጣል "በፍርሃት ይንቀጠቀጣል" አንተ ሞኝ ሰው ሆይ እምነት ያለ ሥራ ምንም ዋጋ እንዳሌለው ማወቅ ትፈልጋለህን? ይህ ጥያቄ ያዕቆብን ለማድመጥ ፈቃደኛ ያልሆነ ሰውን ለመገሰጽ ጥቅም ላይ የዋለ ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡ "አንተ ሞኝ! ያለ ሥራ የሆነ እምነት ጥቅም እንዳሌለው ባረጋግጥልህም ይህንን መስማት ግን አንተ ፈጽሞ አትፈልግም፡፡" (ተመልከት: [[rc:///ta/man/translate/figs-rquestion]])