am_tn/isa/65/17.md

1.1 KiB

አጠቃላይ መረጃ

ያህዌ መናገር ቀጥሏል

እዩ

‹‹ልብ በሉ፤ አስተውሉ››

አዲስ ሰማይና አዲስ ምድር

ሁለቱም በመካከል ያለውን ማንኛውንም ነገር የሚጨምሩ ጽንፎች ናቸው፡፡

ያለፉት ነገሮች አይታሰቡም፤ አይታወሱም

ሁለቱም ሐረጐች ተመሳሳይ ነገር ማለት ሲሆኑ፣ በአንድነት የሆኑት አጽንዖት ለመስጠት ነው፡፡ ይህን በሌላ መልኩ መግለጽ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ባለፈው ጊዜ የሆነውን አታስቡትም››

እናንተ ደስ ይላችኃል

‹‹እናንተ›› የሚያመለክተው የእግዚአብሔር ባርያዎችን ሁሉ ነው፡፡

የልቅሶና የጩኸት ድምፅ ከእንግዲህ እርሷ ውስጥ አይሰማም

ይህን በሌላ መልኩ መግለጽ ትችላለህ፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ከእንግዲህ በእርሷ ውስጥ የጭንቀት ለቅሶና ጩኸት አይሰማም››