am_tn/isa/64/10.md

1.1 KiB
Raw Permalink Blame History

አጠቃላይ መረጃ

የእስራኤል ሕዝብ ለያህዌ መናገር ቀጥለዋል፡፡

የተቀደሱ ከተሞችህ ምድር በዳ ሆኑ

ይህ አጽንዖት የሚሰጠው ከተሞቹ መደምሰሳቸውንና የሚኖርባቸውም እንደሌለ ነው፡፡

አባቶቻችን አንተን ያመሰገኑበት የተቀደሰውና ያማረው ቤተ መቅደሳችን በእሳት ተደምስሶአል፡፡

ይህን በሌላ መልኩ መግለጽ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹አባቶቻችን አንተን ያመሰገኑበትን የተቀደሰውንና ያማረውን ቤተ መቅደሳችንን ጠላት በእሳት አውድሞታል››

ያህዌ ለምን ዝም ትላለህ፤ ለምን ዝም ትላለህ እኛን በማዋረድም ትጸናለህ?

እግዚአብሔር እነርሱን ለመርዳት ባለ መምጣቱ ተስፋ መቁረጣቸውን ለመግለጽ በጥያቄዎች ተጠቅመዋል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ያህዌ እባክህ ዝም አትበል፤ እባክህ ዝም አትበለን እኛንም አታዋርደን!