am_tn/isa/63/17.md

1.2 KiB

አጠቃላይ መረጃ

የእስራኤል ሕዝብ መናገር ቀጥለዋል፡፡

ያህዌ ለአንተ ከመታዘዝ ከመንገድህ እንድንወጣ፣ ልባችንንም እንድናደነድን ለምን አደረግህኸን?

ጸሐፊው ጥያቄውን ያቀረበው የእግዚአብሔርን ሕዝብ ማጉረምረም ለማመልከት ነው፡፡ ይህን ጥያቄ በዐረፍተ ነገር መተርጐም ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ያህዌ ለአንተ እንዳንታዘዝ ከመንገድህ እንድንወጣና እልኸኞች እንድንሆን አደረግኸን››

ለምን ከመንገድህ እንድንወጣ አደረግኸን?

የያህዌን ትእዛዝ አለመፈጸም ከትክክለኛው መንገድ መውጣት እንደሆነ ተነግሯል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ለምን ትክክል ያልሆነ ነገር እንድናደርግ አደረግኸን››

ልባችንን አደነደንህ

ይህ ማለት ለመስማትና ለመታዘዝ ባለ መፈለግ የያህዌን ትምህርት መቃወም ማለት ነው፡፡ እዚህ ላይ፣ ‹‹ልብ›› ዝንባሌን፣ ፍላጐትንና ስሜትን ይወክላል፡፡