am_tn/isa/63/15.md

1.2 KiB

አጠቃላይ መረጃ

የእስራኤል ሕዝብ መናገር ቀጥሎዋል

ቅንዓትህና ታላቅ ሥራህ የት አለ?

እግዚአብሔር እየረዳቸው ስለማይመስል ጥልቅ ስሜቱን ለመግለጽ ጸሐፊው ጥያቄ ያነሣል፡፡ ጥያቄውን በዐረፍተ ነገር መተርጐም ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ቅንዓትህንና ታላቅ ሥራህን አላየንም››

ቸርነትህና ርኅራኄህ ከእኛ ርቀዋል

ይህን በሌላ መልኩ መግለጽ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ቸርነትህንና ርኅራኄኅን ከእኛ አርቀሃል››

አብርሃም ባያውቀን፣ እስራኤልንም ባይገነዘበን

በጣም ተለውጠው ስለ ነበር እነዚህ የእስራኤል ሕዝብ አባቶች ዘሮቻቸውን ማወቅ አልቻለም፡፡ ‹‹አብርሃም›› እና፣ ‹‹ያዕቆብ›› ከረጅም ጊዜ በፊት የነበረውን ሕዝብ ይወክላሉ፡፡

እስራኤል

ይህ እግዚአብሔር ለ፣ ‹‹ያዕቆብ›› የሰጠውን ስም ያመለክታል፡፡