am_tn/isa/63/01.md

1.1 KiB

ይህ ከኤዶም… ከባሶራ የሚመጣ ማን ነው?

ኢሳይያስ የእስራኤል ጠላት ኤዶም ላይ የሚመጣውን የያህዌን ፍርድ ለማመልከት እንደ ጠባቂ በጥያቄና መልስ መልክ ይጠቀማል፡፡ ጥያቄውን በዐረፍተ ነገር መተርጐም ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹እኔ ያህዌ ከኤዶም ቀይ ለብሼ ከባሶራ እመጣለሁ››

ባሶራ

ይህ የኤዶም ዋና ከተማ ነው፡፡

እኔ ነኝ

‹‹እኔ›› ያህዌን ይወክላል፡፡

ልብስህ ለምን ቀይ ሆነ… በወይን መጥመቂያ

ይህን ጥያቄ በዐረፍተ ነገር መተርጐም ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ልብስህ ላይ ያለው ቀይ በወይን መጥመቂያ የነበርህ ሰው አስመስሎሃል››

ወይን መርገጫ

የወይን መርገጫ ዐለት ውስጥ የተፈለፈለ ጐድጓዳ ነገር ሲሆን፣ የወይን ጠጅ እንዲወጣ ሰዎች የወይን ፍሬዎቹን የሚረግጡበት ነው፡፡