am_tn/isa/62/10.md

1.2 KiB

ወዲህ ኑ፤ በበሩ በኩል ኑ

‹‹ኑ›› የሚለው የተደጋገመው አስቸኳይ መሆኑን ለማሳየት ነው፡፡

ሥሩ፣ አውራ መንገዱን ሥሩ

‹‹ሥሩ›› የሚለው ቃል የተደገመው ያህዌ ባስቸኳይ መንገዱ እንዲስተካከል መፈለጉን አጽንዖት ለመስጠት ነው፡፡ ‹‹አውራ መንገድ›› ሕዝቡ የሚመለስበትን መንገድ ይወክላል፡፡ ይህ ከኢሳይያስ 40፥3 እና ኢሳይያስ 57፥14 ጋር ይመሳሰላል፡፡

ድንጋዮች ሰብስቡ

‹‹መንገዱን ለስላሳ ለማድረግ ድንጋዮቹን አውጡ›› ድንጋይ በፍጥነት ለመራመድ እንቅፋት የሆኑ ነገሮችን ሁሉ ይወክላል፡፡

ለሕዝቦች የምልክት ባንዲራ አንሡ

የምልክት ባንዲራ የሌሎችን ትኩረት መሳብ ያመለክታል፡፡ ይህም ማለት የሌሎች አገሮች ሰዎች የእስራኤልን ምድርና አድርግላቸዋለሁ እንዳለው ያህዌ የፈጸመውን ልብ እንዲሉ ያህዌ ሕዝቡን እየጠራ ነው ማለት ነው፡፡