am_tn/isa/62/08.md

1.0 KiB

በቀኝ እጁና በብርታቱ ክንድ

የቀኝ እጅና ክንድ ኀይልና ሥልጣንን ይወክላሉ፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹በኀይልና በሥልጣኑ››

ከእንግዲህ መብል እንዲሆናቸው እህልሽን ለጠላቶችሽ በእርግጥ አልሰጥም

ይህ ማለት ጠላቶቻቸው የእስራኤልን ሕዝብ አያሸንፉም፣ ከእንግዲህ እህላቸውን አይወስዱም ማለት ነው፡፡ ምናልባትም ጠላቶች በግብር መልክ ወይም ሰራዊታቸውን ለመመገብ ባለፈው ጊዜ እህላቸውን ወስደው ሊሆን ይችላል፡፡

ከእንግዲህ መብል እንዲሆናቸው እህልሽን ለጠላቶችሽ በእርግጥ አልሰጥም… ባዕዳንም አዲሱን ወይን ጠጅሽን አይጠጡም፡፡

እነዚህ ዐረፍተ ነገሮች በአንድነት የተቀመጡት አጽንዖትና ለመስጠትና መጠናቀቅን ለማመልከት ነው፡፡